
የሲቄ ውሜንስ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ዳይሬክተር
ወ/ሮ ዘርትሁን ተፈራ


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንና ሲቄ ውሜንስ ዴቨሎፕመንት አሶስዬሽን በመተባበር “ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ተግባራት ለሀብት ማሰባሰብ” (Local Resource Mobilization through local Philanthropies) በሚል አጅንዳ በ13/08/18 ቀን በ Interluxury ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅተዋል።
ለውይይቱ የቀረቡ አጀንዳዎች
1. የሲቄ ውሜንስ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘርትሁን ተፈራ የድርጅቱን ዓላማና ዋና ዋና ክንውኖችን አብራርተዋል።
2. ሲቪል ማህብራት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ “Government Initiatives on Local Fundraising & Resource Mobilization” በሚል ርዕስ ለዘርፉ መጠናከር በመንግሰት በኩል ያለውን ጥረትና ድጋፍ አቀርቧል።
3. ዶ/ር ሙሉጌታ ጌቱ፣ ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት “Background & Concept of Local Resource Mobilization through Local Philanthropy” በሚል ርዕስ የመነሻ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሄዷል።
የፖሊሲና የሕግ ድጋፍ
በአሁኑ ወቅት ያለው የመንግስት ፖሊሲና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ——– መሠረት የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከሀገር ውስጥ ሀብት እንዲያሰባስቡና በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ሰፊ የሕግ ድጋፍ የሰጠ በመሆኑ፣ የዚህ አጀንዳ ውይይትና የግብረ-ኃይሉ መቋቋም ለዘርፉ መጠናከር ትልቅ ዕድል መሆኑ ተመላክቷል።
የመድረኩ ውሳኔ ቀጣይ አቅጣጫ
በመድረኩ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ጉዳዩ ሚመለከታቸውን የመንግስት ተቋማት፣የልማት ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማት፤ የሃይማኖት ተቋማትንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሀገር በቀል ሀብት ማሰባሰብ ትግበራ ግብረ ኃይል (Local Resource Mobilization Working Group) እንዲቋቋም ተወስኖአል።

የግብረ ኃይሉ መቋቋም ዓላማዎች
የግብረ ኃይሉ መቋቋም ዋና ዓላማ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለልማትና ለሰብሐዊ ድጋፍ አሰባሰብ የውጭ ዕርዳታን ዋና የገቢ ምንጫቸው ማድረግን መቀነስ ቢቻልም ለማስቀረት ትልቅ ትኩረት አድርጎ መሥራት ሲሆን የሚከተሉትን ጠቀሜታዎች እንዳሉት ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡-
1. ከውጭ ዕርዳታ ጥገኝነት መውጣት የልማት ስራዎች ዘላቂነትና አስተማማኝ መሰረት እንዲኖራቸው ያደርጋል።
2. ሀገራዊ ችግሮችን በሀገር በቀል አቅም መፍታት የዜጎችንና የተቋማትን የባለቤትነት ስሜት ያሳድጋል።
3. በሀገር በቀል ተዋናዮች መካከል ተያያዥነትና ትስስር ያለው እቀም ይፈጥራል፡፡
4. ሀገራዊ ሀብት ምንጭ መጠቀም በሀገራዊ ልማትና ሰብሐዊ ድጋፎች ላይ አስተዳደራዊና በነጻነት የመወሰን አቅምን ያጎለብታል።


ማጠቃለያ
የሚቋቋመው ግብረ ኃይል፣ የሲቪል ማህበረሰቡን የፋይናንስ አቅም በማጠናከር ለሀገራዊ ልማትና እድገት ሰብሐዊ ድጋፍ ሰፊና አስተማማኝ መሠረት ሊሆን የሚችል የላቀ ሚና ይኖረዋል፡፡

Leave A Comment