Preloader Close

የጄትሮ አመራር ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለሲቄ ሠራተኞች ለዘላቂ ማህበራዊ ኢንተርፕራይዞች እና የፋይናንስ ነፃነት ችሎታ እንዲኖራቸዉ አደረገ::

 

የጄትሮ አመራር ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከሲቄ የሴቶች ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ለሲቄ ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የስልጠና መርሃ ግብር ተጠናቀቀ።    

ነሐሴ 19 እና 23 በተቋሙ ዋና መ/ቤት “Mindset for Business Environment and Grant Seeking” በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት የፈጀው የፊት ለፊት ስልጠና ተጠናቋል።  የስልጠናው ዋና አላማ በአለም አቀፍ ለጋሾች የገንዘብ ድጋፍ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና ድርጅታዊ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ የሲቄ የሴቶች ልማት ማህበር ማህበራዊ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም ድጋፍ ማድረግ ሲሆን። መርሀ ግብሩ ሽንፈትን ሳይፈራ በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች በአንድ ጊዜ በመሰማራት ተጨማሪ እና ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ለማሳየት ያለመ ነው።   

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የሲቄ ሴቶች ልማት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘርትሁን ተፈራ እንዲህ አይነት ስልጠና የሲቄ ሰራተኞች ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግራቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። በግልም በተቋምም ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ገልፀዉ ሁሉም ተሳታፊዎች በክፍለ-ጊዜው በንቃት እንዲሳተፉ አበረታትተዋል።  

                              W/ro Zertihun Tefera delivering the opening speech.

በስልጠናው ወቅት ከቀረቡት አንዱ ቁልፍ ሃሳብ ከቋሚ አስተሳሰብ ወደ የእድገት አስተሳሰብ (ከFixed Mindset ወደ Growth Mindset) በመሸጋገር የተሻሉ እድሎች እንደሚኖሩ በማመን እና ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ የግል አቅምን በማዳበር በሂደት አእምሮአችንን በማለማመድ ማሻሻል እንደሚቻል ተገልፅል። እንዲሁም ስልጠናው ተሳታፊዎች በፈጠራ እንዲያስቡ፣ ስልታዊ በሆነ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ እና በልበ ሙሉነት ከለጋሾች የገንዘብ ድጋፍ ወደ አማራጭ የገቢ ምንጮች እንዲሸጋገሩ ለማድረግ ያለመ ነው።

 

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎች አወንታዊ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን ክፍለ-ጊዜዎቹ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው እና በራስ የመተማመን መንፈስ በማዳበር ወደፊት እንዲራመዱ እንደረዳቸው ጠቁመዋል።  

                                                                 Staff attentively participating in the training  session.

በመጨረሻም በስልጠናዉ መዝጊያ ላይ የሲቄ ሴቶች ልማት ማህበር የፕሮግራም ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ገለልቻ ነጋሳ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በስልጠናው የተማሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባር ለመቀየር እና ለነዚህ አላማዎች በትጋት እንዲሰሩ ሁሉም የሲቄ ሰራተኞች ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

                                   Ato Gelalcha Negassa delivering the closing speech.

ይህ በእንዲህ እንዳለ የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ብሩክ ሞላ በቀጣይ ሁሉም የሲቄ ሰራተኞች በየአካባቢያቸው ያሉ እድሎችን ያለማቋረጥ እንዲፈልጉ እና ያለውን ሃብት በልበ ሙሉነት ወደ ንግዱ ዘርፍ እንዲገቡ አሳስበዉ የሁለት ቀን የገፅ ለገፅ ስልጠናዉ በዚህ መልኩ መጠናቀቁን እና በቀጣይ የአንድ ቀን የበይነ መረብ ክፍለ ጊዜ ስልጠና በGrant Seeking Landscape ዙሪያ እንደሚሰጥ ለተሳታፊዎቹ በማስታወቅ ተጠናቋል።     

Leave A Comment